2 ሳሙኤል 22:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደጋፊዬ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ድጋፍ ሆነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ ጌታ ግን ደገፈኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በተቸገርኩበት ጊዜ በጠላትነት ተነሡብኝ በመከራዬ ቀን መጡብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ጠበቀኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፥ እግዚአብሔር ግን ደገፋዬ ሆነ። |
ሙታን ይነሣሉ፤ በመቃብር ያሉም ይድናሉ። በምድርም የሚኖሩ ደስ ይላቸዋል፤ ከአንተ የሚገኝ ጠል መድኀኒታቸው ነውና፤ የኃጥኣንንም ምድር ታጠፋለህ።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፤ እረዳህማለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ማን ነው? የባሪያውንም ቃል ይስማ፤ በጨለማም የምትሄዱ፥ ብርሃንም የሌላችሁ በእግዚአብሔር ስም ታመኑ፤ በእግዚአብሔርም ተደገፉ፤