መሰወርያውን ጨለማ አደረገ፤ በዙሪያውም የነበረውን ድንኳን የውኃ ጨለማ አደረገ፤ በደመናም አገዘፈው።
ጨለማው በዙሪያው እንዲከብበው፣ ጥቅጥቅ ያለውም የሰማይ ዝናም ደመና እንዲሰውረው አደረገ።
ሁለንተናውን በጨለማ ሰወረ፥ በውሃ በተሞላ ጥቅጥቅ ደመና፥ ራሱን ከበበ።
ሁለንተናውን በጨለማ ሸፈነ። በውሃ የተሞላ ጥቅጥቅ ያለ ደመና ከቦታል።
መሰወርያውን ጨለማ፥ በዙሪያውም የነበረውን ድንኳን፥ በደመና ውስጥ የነበረ የጨለማ ውኃ አደረገ።
ሰማዮችን አዘነበለ፤ ወረደም፤ ጭጋግም ከእግሩ በታች ነበረ።
የጾም አዋጅም ነገሩ፤ ናቡቴንም በሕዝቡ ፊት በከፍተኛ ቦታ አስቀመጡት።
አንድ ሰው የደመናውን መዘርጋት፥ ወይም የማደሪያውን ልክ ቢያውቅ፥
ወደ እግዚአብሔር ሥራ ወደ እጆቹም ተግባር አላሰቡምና አፍርሳቸው፥ አትሥራቸውም።
እግዚአብሔር ማዳኑን አሳየ። በአሕዛብም ፊት ቃል ኪዳኑን ገለጠ።