ከራፋይም ወገን የነበረው ኤስቢ መጣ፤ የጦሩም ሚዛን ክብደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣሪያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊትንም ሊገድለው ፈለገ።
2 ሳሙኤል 21:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም በጌት ላይ ጦርነት ሆነ፤ በዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስትሁላሁሉ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እርሱ ደግሞ ከራፋይም የተወለደ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገና ጋት ላይ በተደረገው ጦርነት በእያንዳንዱ እጁና በእያንዳንዱ እግሩ ስድስት ስድስት ጣቶች በአጠቃላይ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከራፋይም ዘር ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደገና ጌት ላይ በተደረገው ጦርነት በእያንዳንዱ እጁና በእያንዳንዱ እግሩ ስድስት ስድስት ጣቶች ባጠቃላይ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ግዙፍ ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከራፋይም ዘር ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ በጋት ላይ ጦርነት ተደረገ፤ በዚያም ጦርነት የሚወድ አንድ ኀያል ሰው ነበረ፤ ያም ኀያል ሰው በእጆቹና በእግሮቹ ስድስት ስድስት ጣቶች ነበሩት፤ እርሱም ከራፋይም የተወለደ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በጌት ላይ ሰልፍ ሆነ፥ በዚያም በእጅና በእግሩ ስድስት ስድስት ሁላሁሉ ሀያ አራት ጣቶች የነበሩት አንድ ረጅም ሰው ነበረ፥ እርሱ ደግሞ ከራፋይም የተወለደ ነበረ። |
ከራፋይም ወገን የነበረው ኤስቢ መጣ፤ የጦሩም ሚዛን ክብደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣሪያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊትንም ሊገድለው ፈለገ።
ከዚህም በኋላ እንደ ገና በጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት ሆነ፤ ያን ጊዜም አስጣጦታዊው ሴቤኮይ ከራፋይም ወገን የሆነውን ሳፍን ገደለው።
ደግሞ በጌት ላይ ሰልፍ ሆነ ፤ በዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስት ጣቶች በጠቅላላው ሃያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከኀያላን የተወለደ ነበረ።