የሶርህያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ብላቴኖች ከኬብሮን ወጥተው በገባዖን ውኃ መቆሚያ አጠገብ ተገናኙአቸው፤ በውኃውም መቆሚያ በአንዱ ወገን እነዚህ፥ በሌላውም ወገን እነዚያ ሆነው ተቀመጡ።
2 ሳሙኤል 20:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገባዖንም ወዳለው ወደ ታላቁ ድንጋይ በደረሱ ጊዜ አሜሳይ በፊታቸው መጣ፤ ኢዮአብም የሰልፍ ልብስ ለብሶ ነበር፤ በላዩም መታጠቂያ ነበረ፤ በወገቡም ላይ ሰገባ ያለው ሰይፍ ታጥቆ ነበር፤ እርሱም ሲራመድ ሰይፉ ወደቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገባዖን ከታላቁ ቋጥኝ አጠገብ ሳሉ፣ አሜሳይ ሊገናኛቸው መጣ፤ ኢዮአብ የጦር ሜዳ ልብሱን ለብሶ ሰይፉን ከነሰገባው በወገቡ ላይ ታጥቆ ነበር፤ ወደ ፊት ራመድ እንዳለም ሰይፉ ከሰገባው ወጥቶ ወደቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በገባዖን ከታላቁ ቋጥኝ አጠገብ እንደ ደረሱ፥ አማሳይ ሊገናኛቸው መጣ፤ ኢዮአብ የጦር ሜዳ ልብሱን ለብሶ ሰይፉን ከሰገባው በወገቡ ላይ ታጥቆ ነበር፤ ወደ ፊት ራመድ እንዳለም ሰይፉ ከሰገባው ወጥቶ ወደቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በገባዖን ወደሚገኘው ወደ ትልቁ ድንጋይ በደረሱ ጊዜ ዐማሣ አገኛቸው፤ በዚህን ጊዜ ኢዮአብ ሰይፉን በሰገባው ከቶ፥ ሰገባውንም በመታጠቂያው ላይ አስሮ ለጦርነት ተዘጋጅቶ ነበር፤ እየተራመደ ወደ ፊት ሲሄድ ሳለም ሰይፉ ወደቀ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገባዖንም ወዳለው ወደ ታላቁ ድንጋይ በደረሱ ጊዜ አሜሳይ ሊገናኛቸው መጣ፥ ኢዮአብም የሰልፍ ልብስ ለብሶ ነበር፥ በላዩም መታጠቂያ ነበረ፥ በወገቡም ላይ ሰገባ ያለው ሰይፍ ታጥቆ ነበር፥ እርሱም ሲራመድ ሰይፉ ወደቀ። |
የሶርህያ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ብላቴኖች ከኬብሮን ወጥተው በገባዖን ውኃ መቆሚያ አጠገብ ተገናኙአቸው፤ በውኃውም መቆሚያ በአንዱ ወገን እነዚህ፥ በሌላውም ወገን እነዚያ ሆነው ተቀመጡ።
ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም በሰልፍ በገባዖን ወንድማቸውን አሣሄልን ገድሎ ነበርና አበኔርን ይገድሉት ዘንድ ይጠባበቁ ነበር።