ሴቲቱም፥ “ኢዮአብ አንተ ነህን?” አለችው። እርሱም፥ “እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርስዋም፥ “የባሪያህን ቃል ስማ” አለችው። ኢዮአብም፥ “እሰማለሁ” አላት።
2 ሳሙኤል 20:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም እንዲህ አለች፥ “የቀደሙ ሰዎች በእስራኤል ዘንድ አማኞች በሚያስቡት ነገር ተሳስተው እንደ ሆነ በአቤልና በዳን በእውነት ይጠይቁ ይባል ነበር፤ በርግጥም በዚህ ዐይነት ነገር ከተሳሳቱ በአቤል ይጠይቁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ በመቀጠልም እንዲህ አለች፤ “በቀድሞው ጊዜ ሰዎች፣ ‘ምክርን ከአቤል ጠይቁ’ ይሉ ነበር፤ ታዲያ እንዳሉትም ይፈጸም ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያ በመቀጠልም እንዲህ አለች፤ “በቀድሞው ጊዜ ሰዎች፥ ‘ምክርን ከአቤል ጠይቁ’ ይሉ ነበር፤ ነገሩም እንዳሉት ይፈጸም ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም እንዲህ አለችው፤ “በድሮ ዘመን ‘ወደ አቤል ከተማ ሄዳችሁ የጥያቄአችሁን መልስ ከዚያ ታገኛላችሁ’ ይባል ነበር፤ ሰዎችም የሚያደርጉት ይህንኑ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም፦ ቀድሞ፦ የሚጠይቅ በአቤል ዘንድ ይጠይቅ ይባል ነበር፥ እንዲሁም ነገሩ ይፈጸም ነበር። |
ሴቲቱም፥ “ኢዮአብ አንተ ነህን?” አለችው። እርሱም፥ “እኔ ነኝ” ብሎ መለሰላት። እርስዋም፥ “የባሪያህን ቃል ስማ” አለችው። ኢዮአብም፥ “እሰማለሁ” አላት።
በእስራኤል ኀያላን ዘንድ ሰላምን ከሚወድዱት አንድዋ ነኝ፤ አንተ ግን በእስራኤል ያለችውን ከተማና እናት ከተማን ለማፍረስ ትሻለህ፤ ስለምንስ የእግዚአብሔርን ርስት ታጠፋለህ?”