2 ሳሙኤል 2:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አበኔርም ወደ ኋላው ተመልሶ፥ “አንተ አሣሄል ነህን?” አለው። እርሱም፥ “አዎ፥ እኔ ነኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አበኔርም ወደ ኋላው ዘወር ብሎ በመመልከት፣ “አሣሄል! አንተ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አበኔርም ወደ ኋላው ዘወር ብሎ በመመልከት፥ “አሣሄል! አንተ ነህ?” ሲል፥ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አበኔርም፥ ወደ ኋላው መለስ ብሎ “ዐሣሄል፥ አንተ ነህ?” አለ። ዐሣሄልም “አዎ እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አበኔርም ዘወር ብሎ ተመለከተና፦ አንተ አሣሄል ነህን? አለ። እርሱም፦ እኔ ነኝ አለ። |
አበኔርም፥ “ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ ፈቀቅ በል፤ ከብላቴኖቹም አንድ ጐልማሳ ያዝ፤ መሣሪያውንም ለራስህ ውሰድ” አለው። አሣሄል ግን እርሱን ከማሳደድ ፈቀቅ ይል ዘንድ እንቢ አለ።