2 ሳሙኤል 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሳኦል ልጅ ለኢያቡስቴ ከብንያም ልጆች ዐሥራ ሁለት፥ ከዳዊትም ብላቴኖች ዐሥራ ሁለት ተቈጥረው ተነሡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ከብንያም ለሳኦል ልጅ ለኢያቡስቴ ዐሥራ ሁለት፣ ለዳዊት ደግሞ ዐሥራ ሁለት ሰዎች ተነሥተው ተቈጠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም ለብንያም ወገንና ለሳኦል ልጅ ለኢያቡስቴ ዐሥራ ሁለት፥ ለዳዊት ደግሞ ዐሥራ ሁለት አገልጋዮቹ ተነሥተው ተቆጠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ከብንያም ወገን የኢያቡስቴ ተወካዮች የሚሆኑ ዐሥራ ሁለት ሰዎች ተመርጠው ከዳዊት ወገን ከተመረጡት ዐሥራ ሁለት ሰዎች ጋር ውጊያ ገጠሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለብንያም ወገንና ለሳኦል ልጅ ለኢያቡስቴ አሥራ ሁለት፥ ከዳዊትም ባሪያዎች አሥራ ሁለት ተቆጥረው ተነሡ። |
ሁሉም እያንዳንዱ የወደረኛውን ራስ በእጁ ያዘ፤ ሰይፉንም በወደረኛው ጐን ሻጠ፤ ተያይዘውም ወደቁ። የዚያም ስፍራ ስም “በገባዖን የሸመቁ ሰዎች ድርሻ” ተብሎ ተጠራ፤