2 ሳሙኤል 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴም በእስራኤል ላይ በነገሠ ጊዜ አርባ ዓመት ሆኖት ነበረ፤ ዳዊትን ከተከተሉት ከይሁዳ ወገኖች ብቻ በቀር ሁለት ዓመት ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በእስራኤል ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበረ፤ ሁለት ዓመትም ገዛ። የይሁዳ ቤት ግን ዳዊትን ተከተለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በእስራኤል ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበረ፤ ሁለት ዓመትም ገዛ። የይሁዳ ቤት ግን ዳዊትን ተከተለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበር፤ ሁለት ዓመትም ገዛ። የይሁዳ ነገድ ግን ዳዊትን ተከተለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴም በእስራኤል ላይ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የአርባ ዓመት ሰው ነበረ፥ ሁለት ዓመትም ነገሠ፥ ነገር ግን የይሁዳ ቤት ዳዊትን ተከተለ። |
ዳዊትም ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ፥ “በመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ያጨኋትን ሚስቴን ሜልኮልን መልስልኝ” ብሎ መልእክተኞችን ላከ።