ንጉሡም፥ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” አለ። አኪማሖስም፥ “ኢዮአብ እኔን ባሪያህንና የንጉሡን ባሪያ በላከ ጊዜ ብዙ ሰዎችን አይቻለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰለት።
2 ሳሙኤል 18:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም፥ “ፈቀቅ ብለህ ቁም” አለ፤ እርሱም ፈቀቅ ብሎ ቆመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም፣ “ዕልፍ በልና ቁም” አለው፤ ስለዚህ ዕልፍ ብሎ ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም፥ “እልፍ በልና ቁም” አለው፤ ስለዚህ እልፍ ብሎ ቆመ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡም “እልፍ ብለህ ቁም” አለው። እርሱም እልፍ ብሎ ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም፦ ፈቀቅ ብለህ ቁም አለ፥ እርሱም ፈቀቅ ብሎ ቆመ። |
ንጉሡም፥ “ብላቴናው አቤሴሎም ደኅና ነውን?” አለ። አኪማሖስም፥ “ኢዮአብ እኔን ባሪያህንና የንጉሡን ባሪያ በላከ ጊዜ ብዙ ሰዎችን አይቻለሁ፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቅሁም” ብሎ መለሰለት።
እነሆም፥ ኩሲ መጣ፤ ኩሲም፥ “እግዚአብሔር በላይህ የተነሡትን ሁሉ ዛሬ እንደ ተበቀለልህ ለጌታዬ ለንጉሡ ወሬ አምጥቻለሁ” አለ።