ዳዊትም በሁለት በር መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ዘበኛውም በቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ወጣ፤ ዐይኑንም አቅንቶ ብቻውን የሚሮጥ ሰው አየ።
2 ሳሙኤል 18:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘበኛውም ለንጉሡ ሊነግረው ጮኸ። ንጉሡም፥ “ብቻውን እንደ ሆነ በአፉ ወሬ ይኖራል” አለ። እርሱም ፈጥኖ ቀረበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂውም ተጣራና ይህንኑ ለንጉሡ ነገረው። ንጉሡም፣ “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ። ሰውየውም እየቀረበ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠባቂው ተጣራና ይህንኑ ለንጉሡ ነገረው፤ ንጉሡም፥ “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ ይሆናል” አለ። ሰውየውም እየቀረበ መጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዘበኛውም ድምፁንም በማሰማት ያየውን ለንጉሡ ነገረው፤ ንጉሡም “ብቻውን ከሆነ መልካም ወሬ ይዞ የመጣ መሆን አለበት” አለ፤ ያም ሯጭ ሰው እየቀረበ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘበኛውም ለንጉሡ ሊነግረው ጮኸ። ንጉሡም፦ ብቻውን እንደሆነ በአፉ ወሬ ይኖራል አለ። |
ዳዊትም በሁለት በር መካከል ተቀምጦ ነበር፤ ዘበኛውም በቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ወጣ፤ ዐይኑንም አቅንቶ ብቻውን የሚሮጥ ሰው አየ።
ዘበኛውም ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበኛውም ለደጅ ጠባቂው ጮኾ፥ “እነሆ፥ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰው አየሁ” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ደግሞ ወሬ ይዞ ይሆናል” አለ።