ዳዊትና ሰዎቹም በመንገድ ይሄዱ ነበር፤ ሳሚም በተራራው አጠገብ በአቅራቢያው ይሄድ ነበር፤ ሲሄድም ይረግመው፥ ድንጋይም ይወረውርበት ነበር፤ ትቢያም ይበትንበት ነበር።
2 ሳሙኤል 16:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡና ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ሁሉ ደረሱ፤ ደክመውም ነበር፤ በዚያም ዐረፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡና ዐብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ ለመሄድ ወዳሰቡበት ስፍራ ደረሱ፤ በጣም ደክሟቸው ስለ ነበር በዚያ ዐረፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በጣም ደክሞአቸው ስለ ነበር በዚያ ዐረፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡና ተከታዮቹ ሁሉ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በደረሱ ጊዜ በጣም ደክሞአቸው ስለ ነበር በዚያ ዕረፍት አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡና ከእርሱም ጋር የነበረው ሕዝብ ሁሉ ደክመው ነበር፥ በዚያም ዐረፉ። |
ዳዊትና ሰዎቹም በመንገድ ይሄዱ ነበር፤ ሳሚም በተራራው አጠገብ በአቅራቢያው ይሄድ ነበር፤ ሲሄድም ይረግመው፥ ድንጋይም ይወረውርበት ነበር፤ ትቢያም ይበትንበት ነበር።
ንጉሡ ዳዊትም ወደ በውሪም መጣ፤ እነሆም፥ ሳሚ የሚባል የጌራ ልጅ ከሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየሄደም ይረግመው ነበር።
ደክሞና እጁ ዝሎ ሳለ እወድቅበታለሁ፤ አስፈራውማለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ይሸሻል፤ ንጉሡንም ብቻውን እገድለዋለሁ፤
ማርና ቅቤ፥ በግና ላም ይበሉ ዘንድ ለዳዊትና ከእርሱ ጋር ላሉ ሰዎች አመጡ። ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርበውና ተጠምተው ደክመው ነበርና።