2 ሳሙኤል 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴኖቹም ሁሉ ተከተሉት፤ ኬልቲያውያንና ፌልታውያንም ሁሉ በምድረ በዳ በወይራ ሥር ቆሙ። ሕዝቡም ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእርሱ ጋር ያሉ ሰዎችም ሁሉ ስድስት መቶ ነበሩ። ከእርሱ ጋር ፌልታውያንና ኬልቲያውያን፥ በእግራቸው ከጌት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያንም ነበሩ። በንጉሡም ፊት ይሄዱ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹ ሁሉ፣ ከሊታውያን፣ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጋት ዐብረውት የመጡትን ስድስት መቶ ጋታውያንን ሁሉ ጨምሮ ተሰልፈው በንጉሡ ፊት ዐለፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዮቹ ሁሉ፥ ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጌት አብረውት የመጡትን ስድስት መቶ ጌታውያን ሁሉን ጨምሮ ተሰልፈው በንጉሡ ፊት ዐለፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለሟሎቹ ሁሉ በእርሱ በኩል አለፉ፤ የዳዊት ክብር ዘበኞች የነበሩት ከሪታውያንና ፈሊታውያን፥ እንዲሁም ከጋት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያን በንጉሡ ፊት አለፉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎቹም ሁሉ በፊቱ አለፉ፥ ከሊታውያንና ፈሊታውያንም ሁሉ፥ ከእርሱም በኋላ ከጌት የመጡት ስድስት መቶው ጌታውያን ሁሉ በንጉሡ ፊት አለፉ። |
ዳዊትም ሕዝቡን ከኢዮአብ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከኢዮአብም ወንድም ከሶርህያ ልጅ ከአቢሳ እጅ በታች ሢሶውን፥ ከጌት ሰውም ከኤቲ እጅ በታች ሢሶውን ላከ። ዳዊትም ሕዝቡን፥ “እኔ ደግሞ ከእናንተ ጋር እወጣለሁ” አላቸው።
ኢዮአብም በእስራኤል ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ ነበረ፤ የዮዳሄም ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ አለቃ ነበረ፤
አቢሳና የኢዮአብ ሰዎች ከሊታውያንም፥ ፈሊታውያንም፥ ኀያላኑም ሁሉ ወጥተው ተከተሉት፤ ከኢየሩሳሌምም ወጥተው የቢኮሪ ልጅ ሳቡሄን አሳደዱት።
ዳዊትም የእግዚአብሔርን ታቦተ ሕግ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ ያመጣት ዘንድ አልወደደም፤ ዳዊትም በጌት ሰው በአቢዳራ ቤት አገባት።
ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን የዮዳሄም ልጅ በናያስ ከሊታውያንና ፈሊታውያንም ወረዱ፤ ሰሎሞንንም በንጉሡ በዳዊት በቅሎ ላይ አስቀምጠው ወደ ግዮን ወሰዱት።
ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎችም ተነሥተው ከቂአላ ወጡ፤ ወደሚሄድበትም ይከተሉት ነበር። ሳኦልም ዳዊት ከቂአላ እንደ ሸሸ ሰማ፤ ስለዚህም ከመውጣት ቀረ።
ዳዊትም ሰዎቹን፥ “ሁላችሁ ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም ሰይፉን ታጠቀ፤ አራት መቶ ሰዎችም ዳዊትን ተከትለው ወጡ፤ ሁለት መቶውም በጓዛቸው ዘንድ ተቀመጡ።
ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነቤተሰቡ ከአንኩስ ጋር በጌት ተቀመጡ፤ ከዳዊትም ጋር ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት አቤግያ ሁለቱ ሚስቶቹ ነበሩ።
እንዲህም ሆነ፤ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ሴቄላቅ በገቡ ጊዜ፥ አማሌቃውያን በአዜብ በሰቄላቅም ላይ ዘምተው ነበር፤ ሴቄላቅንም መትተው በእሳት አቃጥለዋት ነበር፥
እኛም በከሊታውያን አዜብ፥ በይሁዳም በኩል፥ በካሌብም አዜብ ላይ ዘመትን፥ ሴቄላቅንም በእሳት አቃጠልናት” አለው።
ዳዊትም ከእርሱም ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ሄዱ፤ እስከ ቦሦር ወንዝ ድረስም መጡ፤ ከእነርሱም የቀሩት በዚያ ተቀመጡ።