La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 13:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ብዙ ኅብር ያለ​ው​ንም ልብስ ለብሳ ነበር፤ የን​ጉሡ ልጆች ደና​ግሉ እን​ዲህ ያለ​ውን ልብስ ይለ​ብሱ ነበ​ርና፤ አገ​ል​ጋ​ዩም አስ​ወ​ጥቶ በሩን ዘጋ​ባት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህም አገልጋዩ አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ ጌጠኛ የሆነና በዚያ ጊዜ ድንግል የሆኑት የንጉሥ ልጆች የሚለብሱትን ዐይነት ልብስ ለብሳ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህም አገልጋዩ አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ በዚያን ጊዜ ድንግል የሆኑት የንጉሥ ልጆች የሚለብሱትን እጅጌ ረዥም የነበረ መጐናጸፊያ ለብሳ ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ትዕማርም የአምኖን አሽከር ከቤት አስወጥቶ በሩን ዘጋባት፤ በዚያን ዘመን ያላገቡ የነገሥታት ልጆች ይለብሱት የነበረውን እጅጌ ረዥም የነበረ መጐናጸፊያ ለብሳ ነበር፤ እርስዋም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ ለብሳው የነበረውን መጐናጸፊያ ቀዳ እጅዋን በራስዋ ላይ በመጫን ድምፅዋን ከፍ አድርጋ እያለቀሰች ሄደች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ብዙ ኅብር ያለውንም ልብስ ለብሳ ነበር፥ እንዲህ ያለውን ልብስ የንጉሡ ልጆች ደናግሉ ይለብሱ ነበርና፥ አገልጋዩም አስወጥቶ በሩን ዘጋባት።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 13:18
7 Referencias Cruzadas  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዮሴፍ ወደ ወን​ድ​ሞቹ በቀ​ረበ ጊዜ የለ​በ​ሳ​ትን በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ቺ​ውን ቀሚ​ሱን ገፈ​ፉት፤


ያዕ​ቆ​ብም ዮሴ​ፍን ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወ​ድ​ደው ነበር፤ እርሱ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደው ነበ​ርና። በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ችም ቀሚስ አደ​ረ​ገ​ለት።


ብዙ ኅብር ያለ​በ​ትን ቀሚ​ሱ​ንም ላኩ፤ ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም አገ​ቡት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህን ልብስ አገ​ኘን፤ ይህ የል​ጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እን​ዳ​ል​ሆነ እስኪ እየው?”


በበር ቁሞ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለ​ው​ንም ብላ​ቴና ጠርቶ፥ “ይህ​ችን ሴት ከፊቴ አስ​ወ​ጥ​ተህ በሩን ዝጋ​ባት” አለው።


ናዖ​ድም የእ​ል​ፍ​ኙን ደጅ ዘግ​ቶና ቈልፎ ወደ ውጭ ወጣ።


ምር​ኮ​ውን ሲካ​ፈል፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም ቸብ​ቸቦ ላይ ወዳ​ጆ​ችን ሲወ​ዳጅ ያገ​ኙት አይ​ደ​ለ​ምን? የሲ​ሣራ ምርኮ በየ​ኅ​ብሩ ነበረ፤ የኅ​ብ​ሩም ቀለም የተ​ለ​ያየ ነበረ፤ የማ​ረ​ከ​ውም ወርቀ ዘቦ ግምጃ በአ​ን​ገቱ ላይ ነበረ።