አሁንም ከተማዪቱን እኔ ቀድሜ እንዳልይዝ፥ በስሜም እንዳትጠራ፥ የቀረውን ሕዝብ ሰብስብ፥ ከተማዪቱንም ከብበህ ቀድመህ ያዛት።”
2 ሳሙኤል 12:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ሕዝቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ራባት ሄደ፤ ወግቶም ያዛት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዳዊት መላውን ሰራዊት አሰባስቦ ወደ ረባት በመሄድ ወግቶ ያዛት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ዳዊት መላውን ሠራዊት አሰባስቦ ወደ ራባ በመሄድ ወግቶ ያዛት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊት ሠራዊቱን ሁሉ አሰባስቦ ወደ ራባ በመዝመት አደጋ ጥሎ ያዛት፤ |
አሁንም ከተማዪቱን እኔ ቀድሜ እንዳልይዝ፥ በስሜም እንዳትጠራ፥ የቀረውን ሕዝብ ሰብስብ፥ ከተማዪቱንም ከብበህ ቀድመህ ያዛት።”
የንጉሣቸውንም የሜልኮምን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ያህል ነበር፤ ክቡር ዕንቍም ነበረበት፤ ዳዊትም በራሱ ላይ አደረገው። ከከተማዪቱም እጅግ ብዙ ምርኮ አወጣ።
ዳዊትም ወደ ምናሄም በመጣ ጊዜ በአሞን ልጆች ሀገር በአራቦት የነበረ የነዓሶን ልጅ ኡኤሴብ፥ የሎዶባርም ሰው የአሜሄል ልጅ ማኪር፥ የሮጌሌምም ሰው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ፥