ለድሃው ግን ከገዛት አንዲት ታናሽ በግ በቀር አንዳች አልነበረውም፤ አሳደጋትም፤ ተንከባከባትም፤ ከእርሱና ከልጆቹ ጋር አደገች፤ ከእንጀራውም ትበላ፥ ከዋንጫውም ትጠጣ፥ በብብቱም ትተኛ ነበረ፤ እንደ ልጁም ነበረች።
2 ሳሙኤል 11:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፥ “የኤልያብ ልጅ የኬጤያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ሰው ልኮ ስለ ሴቲቱ አጠያየቀ። ሰውየውም፣ “ይህች የኤልያብ ልጅ፣ የኬጢያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ሰው ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ። እርሱም፥ “ይህች የኤሊዓም ልጅ፥ የሒታዊው የኦርዮን ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን?” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ማንነትዋን ለማወቅ ዳዊት አንድ መልእክተኛ ልኮ ቤርሳቤህ ተብላ የምትጠራው የኤሊዓም ልጅ፥ የሒታዊው የኦርዮ ሚስት መሆንዋን ተረዳ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ልኮ ስለ ሴቲቱ ጠየቀ፥ አንድ ሰውም፦ ይህች የኤልያብ ልጅ የኬጢያዊው የኦርዮ ሚስት ቤርሳቤህ አይደለችምን? አለ። |
ለድሃው ግን ከገዛት አንዲት ታናሽ በግ በቀር አንዳች አልነበረውም፤ አሳደጋትም፤ ተንከባከባትም፤ ከእርሱና ከልጆቹ ጋር አደገች፤ ከእንጀራውም ትበላ፥ ከዋንጫውም ትጠጣ፥ በብብቱም ትተኛ ነበረ፤ እንደ ልጁም ነበረች።
ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና።