2 ሳሙኤል 10:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአድርአዛርም የሚገብሩ ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ለእስራኤል ተገዙ፤ ገበሩላቸውም። ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ይረዱ ዘንድ ፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአድርአዛር ሥር የነበሩት ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል መሸነፋቸውን ባዩ ጊዜ ከእስራኤላውያን ጋራ ሰላም መሠረቱ፤ ተገዙላቸውም። ስለዚህም ሶርያውያን ከዚያ በኋላ አሞናውያንን መርዳት ፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሀዳድዔዜር ሥር የነበሩት ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል መሸነፋቸውን ባዩ ጊዜ ከእስራኤላውያን ጋር ሰላም መሠረቱ፤ ተገዙላቸውም። ከዚያም በኋላ ሶርያውያን ዳግመኛ ዐሞናውያንን ለመርዳት ፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሀዳድዔዜር ሥልጣን ሥር የነበሩት ነገሥታት በእስራኤላውያን ድል መመታታቸውን በተገነዘቡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው የእስራኤላውያን ተገዢዎች ሆኑ፤ ከዚያም በኋላ ሶርያውያን ዳግመኛ ዐሞናውያንን ለመርዳት ፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአድርአዛርም የሚገብሩ ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከእስራኤል ጋር ታረቁ፥ ገበሩላቸውም። ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ይረዱ ዘንድ ፈሩ። |
ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮች አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ጠበቀው።
የአድርአዛርም አገልጋዮች በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ታረቁ፤ ተገዙለትም፤ ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ይረዱ ዘንድ እንቢ አሉ።
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
በእነዚያም ወራት ኢያሱ ተመልሶ አሶርን ያዘ፤ ንጉሥዋንም በሰይፍ ገደለ፤ አሶርም አስቀድሞ የእነዚህ መንግሥታት ዋና ከተማ ነበረች።
ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና፤” እያሉ ይናገራሉ።
አዶኒቤዜቅም፥ “የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡ ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ በታች ፍርፋሪ ይለቅሙ ነበሩ፤ እኔ እንዳደረግሁ እግዚአብሔር እንዲሁ መለሰልኝ” አለ። ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰዱት፥ በዚያም ሞተ።