2 ሳሙኤል 1:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀያላን በሰልፍ ውስጥ እንዴት ወደቁ! ዮናታን ሆይ፥ ሌሎችም የተመቱት በኮረብቶችህ ላይ ወደቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኀያላን እንዴት እንዲህ በጦርነት ወደቁ! ዮናታን በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀያላን እንዴት በጦርነት ወደቁ! ዮናታን በኰረብቶችህ ላይ ተወግቶ ሞቷል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በጦርነቱ መካከል ኀያላን እንዴት ወደቁ? ዮናታን በተራሮችህ ላይ ተገድሎ ወድቆአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኃያላንም በሰልፍ ውስጥ እንዴት ወደቁ! ዮናታንም በኮረብቶችህ ላይ ወድቆአል። |
የእስራኤል ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ቀይ ሐርና ጥሩ ግምጃ ያለብሳችሁ ለነበረ፥ በወርቀዘቦም ያስጌጣችሁ ለነበረ ለሳኦል አልቅሱለት።