“ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል፤ እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው፤ የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ።
2 ሳሙኤል 1:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ ይህ በጻድቃን መጽሐፍ ተጽፎአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም የቀስት እንጕርጕሮ የተባለውን ለይሁዳ ሕዝብ እንዲያስተምሩ አዘዘ፤ ይህም በያሻር መጽሐፍ ተጽፏል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳንም ሕዝብ እንዲያስተምሩ አዘዘ፤ እነሆ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፎ ይገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳም ሕዝብ ያጠኑት ዘንድ አዘዘ፤ ቅኔውም በያሻር መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳንም ልጆች ያስተምሩ ዘንድ አዘዘ። እነሆ፥ ይህ በያሻር መጽሐፍ ተጽፎአል። |
“ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል፤ እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው፤ የአባትህ ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስባቸው፤ እነርሱ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩና ለልጆቻቸውም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎኛልና በኮሬብ በተሰበሰባችሁ ጊዜ በፈጣሪያችሁ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ቆማችሁ ንገራቸው።
እግዚአብሔርም ጠላቶቻቸውን እስኪያጠፋ ድረስ ፀሐይና ጨረቃ በየቦታቸው ቆሙ። ይህም እነሆ በዚህ መጽሐፍ በጊዜው ተጻፈ። ፀሐይም በሰማይ መካከል ቆመች፤ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል አልጠለቀችም።