በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ሰዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ በአዩ ጊዜ፥ “የግብፅ ልቅሶ እንዲህ ታላቅ ነውን?” አሉ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም “ላሐ ግብፅ” ብለው ጠሩት፤ እርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ነው።
2 ሳሙኤል 1:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ስለ ሳኦልና ስለ ልጁ ዮናታን ይህን የኀዘን ቅኔ ተቀኘ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም በሳኦልና በልጁ በዮናታን ሞት ምክንያት ይህን የሐዘን እንጕርጕሮ እየተቀኘ አለቀሰ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም በሳኦልና በልጁ በዮናታን ሞት ምክንያት ይህን የኀዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ስለ ሳኦልና ስለ ልጁም ስለ ዮናታን ይህን የሐዘን ቅኔ ተቀኘ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ስለ ሳኦልና ሰለ ልጁ ስለ ዮናታን ይህን የኅዘን ቅኔ ተቀኘ፥ |
በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ሰዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ በአዩ ጊዜ፥ “የግብፅ ልቅሶ እንዲህ ታላቅ ነውን?” አሉ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም “ላሐ ግብፅ” ብለው ጠሩት፤ እርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ነው።
ኤርምያስም ለንጉሡ ለኢዮስያስ የልቅሶ ግጥም ገጠመለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ወንዶችና ሴቶች መዘምራን ሁሉ በልቅሶ ግጥማቸው ስለ ኢዮስያስ ይናገሩ ነበር፤ ይህም በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ወግ ሆኖ በልቅሶ ግጥም ተጽፎአል።
ይኸውም ሙሾ ነው፤ ሙሾን ያሞሹለታል፤ የአሕዛብ ሴቶች ልጆች ያሞሹለታል፤ ስለ ግብፅና ስለ ኀይልዋ ሁሉ ያሞሹለታል፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።