2 ነገሥት 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያም ለምጻሞች ወደ ሰፈሩ መጀመሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ ወደ አንድ ድንኳን ገብተው በሉ፤ ጠጡም፤ ከዚያም ወርቅና ብር ልብስም ወሰዱ፤ ሄደውም ሸሸጉት፤ ተመልሰውም ወደ ሌላ ድንኳን ገቡ፤ ከዚያም ደግሞ ወስደው ሸሸጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለምጽ ያለባቸውም ሰዎች ወደ ሰፈሩ አጠገብ ከደረሱ በኋላ፣ ከድንኳኖቹ ወደ አንዱ ገብተው በሉ፤ ጠጡም፤ ከዚያም ብር፣ ወርቅና ልብስ ይዘው በመሄድ ደበቁት። ተመልሰው በመምጣትም ወደ ሌላው ድንኳን ገብተው ሌሎች ነገሮችን በመውሰድ እንደዚሁ ደበቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አራቱ ሰዎች ወደ ሶርያውያን ሰፈር ዳርቻ በደረሱ ጊዜ ወደ አንድ ድንኳን ውስጥ ገቡ፤ በዚያም ያገኙትን ነገር ሁሉ በልተውና ጠጥተው ያገኙትን ብር፥ ወርቅና ልብስ ይዘው ሄደው ደበቁ፤ እንደገናም ተመልሰው ወደ ሌላ ድንኳን በመግባት እንደዚያው አደረጉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አራቱ ሰዎች ወደ ሶርያውያን ሰፈር ዳርቻ በደረሱ ጊዜ ወደ አንድ ድንኳን ውስጥ ገቡ፤ በዚያም ያገኙትን ነገር ሁሉ በልተውና ጠጥተው ያገኙትን ብር፥ ወርቅና ልብስ ይዘው ሄደው ደበቁ፤ እንደገናም ተመልሰው ወደ ሌላ ድንኳን በመግባት እንደዚያው አደረጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህም ለምጻሞች ወደ ሰፈሩ መጀመሪያ ዳርቻ በመጡ ጊዜ ወደ አንድ ድንኳን ገብተው በሉ፤ ጠጡም፤ ከዚያም ወርቅና ብር ልብስም ወሰዱ፤ ሄደውም ሸሸጉት፤ ተመልሰውም ወደ ሌላ ድንኳን ገቡ፤ ከዚያም ደግሞ ወስደው ሸሸጉ። |
ከዚያም ወዲያ እርስ በርሳቸው፥ “መልካም አላደረግንም፤ ዛሬ የመልካም ምሥራች ቀን ነው፤ እኛ ዝም ብለናል፤ እስኪነጋም ድረስ ብንቆይ በደለኞች እንሆናለን፤ ኑ፥ እንሂድ፤ ለንጉሥ ቤተሰብም እንናገር” ተባባሉ።
ገመዶችሽ ተበጥሰዋል፤ ጥንካሬ የላቸውምና፤ ደቀልሽ ዘመመ፤ ሸራውንም መዘርጋት አልቻለም፤ እስከሚያዝም ድረስ አላማውን አልተሸከመም። በዚያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ተከፈለ፤ ብዙ አንካሶች እንኳ ምርኮውን ማረኩ።
በዚያም የተገኙ ዐሥር ሰዎች ቀርበው እስማኤልን እንዲህ አሉት፥ “በሜዳው ድልብ አለንና፥ ገብስና ስንዴ፥ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን፤” እርሱም በወንድሞቻቸው መካከል እነርሱን መግደል ተወ።
“ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፤ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።
በዘረፋ መካከል አንድ ያማረ ካባ፥ ሁለት መቶ ሰቅል ብር፥ ሚዛኑም አምሳ ሰቅል የሆነ ወርቅ አይቼ ተመኘኋቸው፤ ወሰድኋቸውም፤ እነሆም በድንኳኔ ውስጥ በመሬት ተሸሽገዋል፤ ብሩም ከሁሉ በታች ነው” አለው።