ዘበኛውም ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበኛውም ለደጅ ጠባቂው ጮኾ፥ “እነሆ፥ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰው አየሁ” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ደግሞ ወሬ ይዞ ይሆናል” አለ።
2 ነገሥት 7:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገብተውም በከተማው በር ጮኹ፤ እንዲህም ብለው ተናገሩ፥ “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ገባን፤ እነሆም፥ ፈረሶችና አህዮች ታስረው፥ ድንኳኖችም ተተክለው ነበር እንጂ ያገኘነው አልነበረም፤ የሰውም ድምፅ አልነበረም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሄደው የከተማዪቱን መግቢያ በር ጠባቂዎች ጮኸው በመጥራት፣ “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ገባን፤ እዚያም ከታሰሩ ፈረሶችና አህዮች በቀር አንድም ሰው አልነበረም፤ የማንም ድምፅ አልተሰማም፤ ድንኳኖቹም እንዳሉ ናቸው” ብለው ነገሯቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጥተውም “ወደ ሶርያውያን ሰፈር መጣን፤ እነሆም፥ ፈረሶችና አህዮች ታስረው፥ ድንኳኖችም ተተክለው ነበር እንጂ ሰው አልነበረም፤ የሰውም ድምፅ አልነበረም፤” ብለው ወደ ከተማይቱ ደጅ ጠባቂ ጮኹ። |
ዘበኛውም ሌላ ሰው ሲሮጥ አየ፤ ዘበኛውም ለደጅ ጠባቂው ጮኾ፥ “እነሆ፥ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰው አየሁ” አለ። ንጉሡም፥ “እርሱ ደግሞ ወሬ ይዞ ይሆናል” አለ።
ከዚያም ወዲያ እርስ በርሳቸው፥ “መልካም አላደረግንም፤ ዛሬ የመልካም ምሥራች ቀን ነው፤ እኛ ዝም ብለናል፤ እስኪነጋም ድረስ ብንቆይ በደለኞች እንሆናለን፤ ኑ፥ እንሂድ፤ ለንጉሥ ቤተሰብም እንናገር” ተባባሉ።
ከእነርሱም ጋር በሁለተኛው ተራ የሆኑትን ወንድሞቻቸውን ዘካርያስን፥ ቤንን፥ አዝኤልን፥ ስሜራሞትን፥ ኢያሄልን፥ ኡኒን፥ ኤልያብን፥ በናእያን፥ መዕሤያን፥ መታትያን፥ ኤልፋይን፥ ሜቄድያን፥ በረኞችንም አብዲዶምን፥ ኢያኤልንና ዖዝያስን አቆሙ።
አብዲዶምንም፥ ስድሳ ስምንቱንም ወንድሞቻቸውን፤ የኤዶታምም ልጅ አብዲዶምና ሖሳ በረኞች ይሆኑ ዘንድ ተዋቸው፤