እኔም ከአሞራውያን እጅ በሰይፌና በቀስቴ የወሰድሁትን ምርኮ ለአንተ ከወንድሞችህ የተሻለውን እሰጥሃለሁ” አለው።
2 ነገሥት 6:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “በሰይፍህና በቀስትህ የማረክሃቸውን ግደል እንጂ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክሃቸው አይደሉምና አትግደላቸው። ይልቁንስ እንጀራና ውኃ በፊታቸው አቅርብላቸው፤ በልተውና ጠጥተውም ወደ ጌታቸው ይመለሱ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “አትግደላቸው፤ ለመሆኑ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክሃቸውን ትገድላቸው ዘንድ ይገባሃልን? አሁንም የሚበሉትንና የሚጠጡትን አስቀርብላቸው፤ በልተው ጠጥተውም ወደ ጌታቸውም ይሂዱ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕም “አይሆንም! እንኳን እነዚህን፥ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክኻቸውን ወታደሮች መግደል አይገባህም፤ ይልቅስ የሚበሉትና የሚጠጡትን ምግብ አቅርብላቸውና ወደ ንጉሣቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አድርግ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕም “አይሆንም! እንኳን እነዚህን፥ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክኻቸውን ወታደሮች መግደል አይገባህም፤ ይልቅስ የሚበሉትና የሚጠጡትን ምግብ አቅርብላቸውና ወደ ንጉሣቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አድርግ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም “አትግደላቸው፤ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክኸውን ትገድል ዘንድ ይገባሃልን? እንጀራና ውሃ በፊታቸው አኑርላቸው፤ በልተውና ጠጥተውም ወደ ጌታቸው ይሂዱ፤” አለው። |
እኔም ከአሞራውያን እጅ በሰይፌና በቀስቴ የወሰድሁትን ምርኮ ለአንተ ከወንድሞችህ የተሻለውን እሰጥሃለሁ” አለው።
ነገር ግን የይሁዳን ልጆች ይቅር እላቸዋለሁ፤ እኔ አምላካቸውም እግዚአብሔር አድናቸዋለሁ እንጂ በቀስት ወይም በሰይፍ፥ ወይም በጦር፥ ወይም በሠረገላ፥ ወይም በፈረሶች፥ ወይም በፈረሰኞች የማድናቸው አይደለም” አለው።
በዚያም ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፥ ከመሬትም ተንቀሳቃሾች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ። ቀስትንና ሰይፍን፥ ጦርንም ከምድሩ እሰብራለሁ፤ ተዘልለሽም ትቀመጫለሽ።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
በፊታችሁም ተርብ ሰደድሁ፤ በሰይፍህም፥ በቀስትህም ሳይሆን ዐሥራ ሁለቱን የአሞሬዎናውያንን ነገሥታት ከፊታችሁ አሳደድኋቸው።