2 ነገሥት 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሶርያውያንም ጋር ወደ ሰልፍ በወጣ ጊዜ ከእስራኤል ምድር ታናሽ ብላቴና ሴት ማረከ፤ ለሚስቱም አገልጋይ አደረጋት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አደጋ ጣዮች ከሶርያ ወጥተው፣ ከእስራኤል ምድር አንዲት ልጃገረድ ማረኩ፤ እርሷም የንዕማንን ሚስት ታገለግላት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሶርያውያን በእስራኤላውያን ላይ ወረራ በፈጸሙበት በአንድ ወቅት፥ አንዲት ትንሽ እስራኤላዊት ልጃገረድ ማርከው ወስደው ነበር፤ እርሷም ለንዕማን ሚስት፥ ገረድ ሆና ትኖር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሶርያውያን በእስራኤላውያን ላይ ወረራ በፈጸሙበት በአንድ ወቅት፥ አንዲት ትንሽ እስራኤላዊት ልጃገረድ ማርከው ወስደው ነበር፤ እርስዋም ለንዕማን ሚስት፥ ገረድ ሆና ትኖር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሶርያውያንም አገር አደጋ ጣዮች ወጥተው ነበር፤ ከእስራኤልም ምድር ታናሽ ብላቴና ሴት ማርከው ነበር፤ የንዕማንንም ሚስት ታገለግል ነበር። |
እመቤቷንም፥ “ጌታዬ በሰማርያ ወደሚኖረው ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ነቢዩ ይሄድ ዘንድ በተገባው ነበር፤ ከለምጹም በፈወሰው ነበር” አለቻት።
ብዙም መብል አዘጋጀላቸው፤ በበሉና በጠጡ ጊዜም አሰናበታቸው፤ እነርሱም ወደ ጌታቸው ሄዱ። ከዚያም በኋላ የሶርያውያን አደጋ ጣዮች ዳግመኛ ወደ እስራኤል ሀገር አልመጡም።