አሁንም የሰውየውን ሚስት መልስ፤ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፤ ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንድትሞት፥ ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በርግጥ ዕወቅ።”
2 ነገሥት 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንዕማን ግን ተቈጥቶ ሄደ፤ እንዲህም አለ፥ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚመጣ፥ ቆሞም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፥ የለምጹንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንዕማን ግን ተቈጥቶ እንዲህ በማለት ሄደ፤ “እኔ እኮ በርግጥ ወደ እኔ መጥቶ በመቆም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፣ በእጁም ዳስሶ ከለምጽ በሽታዬ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንዕማን ግን ተቆጥቶ ወደ አገሩ ለመመለስ ተነሣ፤ እንዲህም እያለ ያጉረመርም ነበር፤ “እኔ እኮ ነቢዩ መጥቶ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የቆዳው በሽታ ባረፈበት ገላዬ ላይ እጆቹን በመወዝወዝ ይፈውሰኛል ብዬ አስቤ ነበር! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንዕማን ግን ተቈጥቶ ወደ አገሩ ለመመለስ ተነሣ፤ እንዲህም እያለ ያጒረመርም ነበር፤ “እኔ እኮ ነቢዩ መጥቶ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የቆዳው በሽታ ባረፈበት ገላዬ ላይ እጆቹን በመወዝወዝ ይፈውሰኛል ብዬ አስቤ ነበር! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንዕማን ግን ተቈጥቶ ሄደ፤ እንዲህም አለ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚመጣ፥ ቆሞም የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ፥ የለምጹንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚፈውሰኝ መስሎኝ ነበር። |
አሁንም የሰውየውን ሚስት መልስ፤ ነቢይ ነውና፥ ስለ አንተም ይጸልያል፤ ትድናለህም። ባትመልሳት ግን አንተ እንድትሞት፥ ለአንተ የሆነውም ሁሉ እንዲሞት በርግጥ ዕወቅ።”
እንዲሁም ከእርሱ ሄዳ፥ በሩን ከእርስዋና ከልጆችዋ በኋላ ዘጋች፤ እነርሱም ማድጋዎቹን ወደ እርስዋ ያቀርቡላት ነበር፤ እርስዋም ትገለብጥ ነበር።
ኤልሳዕም፥ “ሂድ፥ በዮርዳኖስም ሰባት ጊዜ ተጠመቅ፤ ሰውነትህም ይፈወሳል፤ አንተም ንጹሕ ትሆናለህ” ብሎ ወደ እርሱ መልእክተኛ ላከ።
የደማስቆ ወንዞች ባብናና ፋርፋ ከእስራኤል ውኆች ሁሉ አይሻሉምን? ሄጄስ በእነርሱ ውስጥ መጠመቅና መንጻት አይቻለኝም ኖሮአልን?” ብሎ በቍጣ ተመልሶ ሄደ።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እኔ የምልከውን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።”
ለሚናገረው እንቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነርሱ በደብረ ሲና የተገለጠላቸውን እንቢ ስለ አሉት ካልዳኑ፥ ከሰማይ ከመጣው ፊታችንን ብንመልስ እኛማ እንዴታ?