La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 4:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ሁም ከእ​ርሱ ሄዳ፥ በሩን ከእ​ር​ስ​ዋና ከል​ጆ​ችዋ በኋላ ዘጋች፤ እነ​ር​ሱም ማድ​ጋ​ዎ​ቹን ወደ እር​ስዋ ያቀ​ር​ቡ​ላት ነበር፤ እር​ስ​ዋም ትገ​ለ​ብጥ ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ትታው ሄዳ መዝጊያውን በራሷና በልጆቿ ላይ የኋሊት ዘጋችው፤ ማድጎቹን እያቀረቡላትም እርሷ ትሞላ ጀመር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህም ሴትዮዋ ወደ ቤትዋ ሄዳ ከልጆችዋ ጋር በሩን ዘጋች፤ ዘይት የነበረበትን ትንሽ ማሰሮ አንሥታ ልጆችዋ እያቀረቡላት በማንቆርቆር በየማድጋዎቹ ሞላች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም ሴትዮዋ ወደ ቤትዋ ሄዳ ከልጆችዋ ጋር በሩን ዘጋች፤ ዘይት የነበረበትን ትንሽ ማሰሮ አንሥታ ልጆችዋ እያቀረቡላት በማንቈርቈር በየማድጋዎቹ ሞላች።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲሁም ከእርሱ ሄዳ በሩን ከእርስዋና ከልጆችዋ በኋላ ዘጋች፤ እነርሱም ማድጋዎቹን ወደ እርስዋ ያመጡ ነበር፤ እርስዋም ትገለብጥ ነበር።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 4:5
6 Referencias Cruzadas  

ወደ ቤት​ሽም ገብ​ተሽ ከአ​ን​ቺና ከል​ጆ​ችሽ በኋላ በሩን ዝጊ፤ ወደ እነ​ዚ​ህም ማድ​ጋ​ዎች ሁሉ ዘይ​ቱን ገል​ብጪ፤ የሞ​ላ​ው​ንም ፈቀቅ አድ​ርጊ” አላት።


ከዚ​ህም በኋላ ልጆ​ች​ዋን፥ “ደግሞ ማድጋ አም​ጡ​ልኝ” አለ​ቻ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ሌላ ማድጋ የለም” አሏት፤ ዘይ​ቱም ቆመ።


ንዕ​ማን ግን ተቈ​ጥቶ ሄደ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ቆሞም የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ፥ የለ​ም​ጹ​ንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚ​ፈ​ው​ሰኝ መስ​ሎኝ ነበር።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የነ​ገ​ሩሽ ቃል እን​ደ​ሚ​ሆን የም​ታ​ምኚ አንቺ ብፅ​ዕት ነሽ።”