La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 4:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኤል​ሳ​ዕም፥ “ዶቄት አም​ጣና በም​ን​ቸቱ ውስጥ ጨም​ረው” አለው፥ ኤል​ሳ​ዕም ግያ​ዝን፥ “ለሕ​ዝቡ መል​ስ​ላ​ቸው ይብሉ” አለው። ከዚ​ህም በኋላ በም​ን​ቸቱ ውስጥ ክፉ ነገር አል​ተ​ገ​ኘም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኤልሳዕም፣ “እስኪ ዱቄት አምጡልኝ” አለ። ያንም በምንቸቱ ውስጥ ጨምሮ፣ “እንዲመገቡት ለሰዎቹ አቅርቡላቸው” አለ። በምንቸቱም ውስጥ ጕዳት የሚያስከትል ነገር አልተገኘም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኤልሳዕም ዱቄት እንዲሰጡት ጠይቆ በድስቱ ውስጥ ጨመረውና “ወጡን እያወጣህ ጨምርላቸው” ሲል አዘዘ፤ በዚህም ጊዜ በወጡ ውስጥ ምንም ዓይነት መራራነት አልነበረም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኤልሳዕም ዱቄት እንዲሰጡት ጠይቆ በድስቱ ውስጥ ጨመረውና “ወጡን እያወጣህ ጨምርላቸው” ሲል አዘዘ፤ በዚህም ጊዜ በወጡ ውስጥ ምንም ዐይነት መራራነት አልነበረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም “ዱቄት አምጡልኝ፤” አለ፤ በምንቸቱም ውስጥ ጥሎ “ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ቅዱ፤” አለ። በምንቸቱም ውስጥ ክፉ ነገር አልተገኘም።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 4:41
7 Referencias Cruzadas  

ውኃው ወዳ​ለ​በ​ትም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለ​በ​ትና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈው​ሼ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ የሚ​ሞት፥ የሚ​መ​ክ​ንም አይ​ኖ​ርም” አለ።


ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሂድ፥ በዮ​ር​ዳ​ኖ​ስም ሰባት ጊዜ ተጠ​መቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህም ይፈ​ወ​ሳል፤ አን​ተም ንጹሕ ትሆ​ና​ለህ” ብሎ ወደ እርሱ መል​እ​ክ​ተኛ ላከ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው፥ “የወ​ደ​ቀው ወዴት ነው?” አለ፤ ስፍ​ራ​ው​ንም አሳ​የው፤ ከእ​ን​ጨ​ትም ቅር​ፊት ቀርፎ በዚያ ጣለው፤ ብረ​ቱም ተን​ሳ​ፈፈ።


ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕን​ጨ​ትን አሳ​የው፤ በው​ኃ​ውም ላይ ጣለው፤ ውኃ​ውም ጣፈጠ። በዚ​ያም ሥር​ዐ​ት​ንና ፍር​ድን አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው፤ በዚ​ያም ፈተ​ና​ቸው።


ይህ​ንም ብሎ በም​ድር ላይ ምራ​ቁን እን​ትፍ አለ፤ በም​ራ​ቁም ጭቃ አድ​ርጎ የዕ​ዉ​ሩን ዐይ​ኖች ቀባው።


ጳው​ሎስ ግን እጁን አራ​ግፎ እፉ​ኝ​ቱን በእ​ሳት ውስጥ ጣላት፤ ጕዳ​ትም አላ​ገ​ኘ​ውም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስን​ፍና ከሰው ይልቅ ይጠ​በ​ባ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበ​ረ​ታ​ልና።