La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 4:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኤል​ሳ​ዕም ወደ ቤት ገብቶ በሩን በሁ​ለቱ ላይ ዘጋ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለየ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደ ውስጥም ገባ፤ ከዚያም በሩን በራሱና በልጁ ላይ ዘግቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከልጁ ጋር ብቻውን ሆኖ፥ ክፍሉንም ዘግቶ፥ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከልጁ ጋር ብቻውን ሆኖ፥ ክፍሉንም ዘግቶ፥ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ገብቶም በሩን ከሁለቱ በኋላ ዘጋ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 4:33
12 Referencias Cruzadas  

ኤል​ሳ​ዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ ሕፃኑ ሞቶ በአ​ል​ጋው ላይ ተጋ​ድሞ ነበር።


ወደ ቤት​ሽም ገብ​ተሽ ከአ​ን​ቺና ከል​ጆ​ችሽ በኋላ በሩን ዝጊ፤ ወደ እነ​ዚ​ህም ማድ​ጋ​ዎች ሁሉ ዘይ​ቱን ገል​ብጪ፤ የሞ​ላ​ው​ንም ፈቀቅ አድ​ርጊ” አላት።


ንዕ​ማን ግን ተቈ​ጥቶ ሄደ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ ወደ እኔ የሚ​መጣ፥ ቆሞም የአ​ም​ላ​ኩን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም የሚ​ጠራ፥ የለ​ም​ጹ​ንም ስፍራ በእጁ ዳስሶ የሚ​ፈ​ው​ሰኝ መስ​ሎኝ ነበር።


ወደ ሰማ​ር​ያም በገቡ ጊዜ ኤል​ሳዕ፥ “አቤቱ፥ ያዩ ዘንድ የእ​ነ​ዚ​ህን ሰዎች ዐይ​ኖች ግለጥ” አለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ገለጠ፤ እነ​ር​ሱም አዩ። እነ​ሆም፥ በሰ​ማ​ርያ መካ​ከል እን​ዳሉ ዐወቁ።


አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ፤ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።


ወደ ቤትም በገባ ጊዜ ከጴ​ጥ​ሮስ፥ ከያ​ዕ​ቆ​ብና ከዮ​ሐ​ንስ፥ ከብ​ላ​ቴ​ና​ይ​ቱም አባ​ትና እናት በቀር ማንም ከእ​ርሱ ጋር ሌላ ሰው ይገባ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደም።


ጴጥ​ሮ​ስም ሁሉን ካስ​ወጣ በኋላ ተን​በ​ር​ክኮ ጸለየ፤ ወደ በድ​ን​ዋም መለስ ብሎ፥ “ጣቢታ ሆይ፥ ተነሽ” አላት፤ እር​ስ​ዋም ዐይ​ኖ​ች​ዋን ገለ​ጠች፤ ያን​ጊ​ዜም ጴጥ​ሮ​ስን አየ​ችው፤ ቀና ብላም ተቀ​መ​ጠች።