2 ነገሥት 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕፃኑም አደገ፤ እህል አጫጆችም ወዳሉበት ወደ አባቱ መጣ። አባቱንም፥ “ራሴን ራሴን” አለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕፃኑ አደገ፤ አንድ ቀንም አባቱ ከዐጫጆች ጋራ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕፃኑም አደገ፤ በመከር ወራት አንድ ቀን ጧት ያ ልጅ ከአጫጆች ጋር በእርሻ ውስጥ ወደነበረው ወደ አባቱ ሄደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕፃኑም አደገ፤ በመከር ወራት አንድ ቀን ጧት ያ ልጅ ከአጫጆች ጋር በእርሻ ውስጥ ወደነበረው ወደ አባቱ ሄደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕፃኑም አደገ፤ አንድ ቀንም እህል አጫጆች ወዳሉበት ወደ አባቱ ወጣ። |
ኤልሳዕም ልጅዋን ያስነሣላትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነሥተሽ ሂጂ፤ በምታገኚውም ስፍራ ተቀመጪ፤ እግዚአብሔር በምድር ራብን ጠርቶአልና፤ ሰባት ዓመትም በምድር ላይ ይቆያል” ብሎ ተናገራት።
እነሆም፥ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፥ አጫጆችንም፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን አላቸው። እነርሱም፦ እግዚአብሔር ይባርክህ ብለው መለሱለት።