ከከተማዪቱም በሰልፈኞች ላይ ተሾመው ከነበሩት አንዱን ጃንደረባ፥ በከተማዪቱም ከሚገኙት በንጉሡ ፊት ከሚቆሙት ሰባቱን ሰዎች፥ የሀገሩን ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከተማዪቱም ከተገኙት የሀገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎችን ወሰደ።
2 ነገሥት 25:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከከተማዪቱም በሰልፈኞች ላይ ተሾመው ከነበሩት አንዱን ጃንደረባ፥ በከተማዪቱም የተገኙትን በንጉሡ ፊት የሚቆሙትን አምስቱን ሰዎች፥ የሀገሩንም ሕዝብ የሚያሰልፍ የሠራዊቱን አለቃ ጸሓፊ፥ በከተማዪቱም ከተገኙት ከሀገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎችን ወሰደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስከዚያች ጊዜ ድረስ በከተማዪቱ ውስጥ ከቀሩትም የተዋጊዎቹን አለቃና ዐምስት የንጉሡን አማካሪዎች ወሰዳቸው። ደግሞም የአገሩን ሕዝብ ለውትድርና የሚመለምለውን ዋና የጦር አለቃ የነበረውን ጸሓፊውንና በከተማዪቱ ውስጥ የተገኙትን የጸሓፊውን ስድሳ ሰዎች ወሰዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነው አንድ ባለ ሥልጣን፥ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ የነበሩትን አምስቱን የንጉሥ አማካሪዎች፥ የአገሩን ሕዝብ ለወታደርነት ይመለምል የነበረውን መኰንንና ሌሎችንም ሥልሳ ሰዎችን ወሰደ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነው አንድ ባለሥልጣን፥ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ የነበሩትን አምስቱን የንጉሥ አማካሪዎች፥ የአገሩን ሕዝብ ለወታደርነት ይመለምል የነበረውን መኰንንና ሌሎችንም ሥልሳ ሰዎችን ወሰደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከከተማይቱም በሰልፈኞች ላይ ተሹመው ከነበሩት አንዱን ጃንደረባ፥ በከተማይቱም የተገኙትን በንጉሡ ፊት የሚቆሙትን አምስቱን ሰዎች፥ የአገሩንም ሕዝብ የሚያሰልፍ የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከተማይቱም ከተገኙት ከአገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎች ወሰደ። |
ከከተማዪቱም በሰልፈኞች ላይ ተሾመው ከነበሩት አንዱን ጃንደረባ፥ በከተማዪቱም ከሚገኙት በንጉሡ ፊት ከሚቆሙት ሰባቱን ሰዎች፥ የሀገሩን ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፥ በከተማዪቱም ከተገኙት የሀገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎችን ወሰደ።