በሣጥኑም ውስጥ የተገኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የንጉሡ ጸሓፊና የካህናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን ገንዘብ ሁሉ ቈጥረው በከረጢት ውስጥ ያኖሩት ነበር።
2 ነገሥት 22:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በንጉሡም በኢዮስያስ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመተ መንግሥት በስምንተኛው ወር ንጉሡ የእግዚአብሔርን ቤት ጸሓፊ የሜሱላምን ልጅ የኤሴልዩን ልጅ ሳፋንን እንዲህ ሲል ላከው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዘመነ መንግሥቱ በዐሥራ ስምንተኛውም ዓመት ኢዮስያስ የሜሶላምን የልጅ ልጅ የኤዜልያስን ልጅ ጸሓፊውን ሳፋንን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ላከው፤ እንዲህም አለው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የመሹላም የልጅ ልጅ፥ የአጻልያ ልጅ የሆነውን የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ሳፋንን ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ወደ ቤተ መቅደስ ላከው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የመሹላም የልጅ ልጅ፥ የአጻልያ ልጅ የሆነውን የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ሳፋንን ከዚህ የሚከተለውን መልእክት ወደ ቤተ መቅደስ ላከው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በንጉሡም በኢዮስያስ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር ንጉሡ ጸሐፊውን የሜሶላምን ልጅ የኤዜልያስን ልጅ ሳፋንን ወደ እግዚአብሔር ቤት ላከው፤ እንዲህም አለው |
በሣጥኑም ውስጥ የተገኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የንጉሡ ጸሓፊና የካህናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን ገንዘብ ሁሉ ቈጥረው በከረጢት ውስጥ ያኖሩት ነበር።
ባሮክም የኤርምያስን ቃል በእግዚአብሔር ቤት በላይኛው አደባባይ በእግዚአብሔር ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሓፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ክፍል በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ በመጽሐፉ አንበበ።
ወደ ንጉሡም ቤት ወደ ጸሓፊው ክፍል ወረደ፤ እነሆም አለቆቹ ሁሉ፥ ጸሓፊው ኤሊሳማ፥ የሸማያ ልጅ ድላያ፥ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፥ የሳፋን ልጅ ገማርያ፥ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ፥ አለቆቹም ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።