ውኃው ወዳለበትም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ የሚሞት፥ የሚመክንም አይኖርም” አለ።
2 ነገሥት 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ነገር ውኃው ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልሳዕ እንደ ተናገረውም ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ የተፈወሰ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ኤልሳዕ በተናገረው መሠረት ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ ንጹሕ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ኤልሳዕ በተናገረው መሠረት ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ ንጹሕ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ነገር ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ ተፈውሶአል። |
ውኃው ወዳለበትም ምንጭ ወጥቶ ጨው ጣለበትና፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ውኃ ፈውሼዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ የሚሞት፥ የሚመክንም አይኖርም” አለ።
ከዚያም ወደ ቤቴል ወጣ፤ በመንገድም ሲወጣ ልጆች ከከተማዪቱ ወጥተው፥ “አንተ ራሰ በራ! ውጣ! አንተ ራሰ በራ! ውጣ” ብለው አፌዙበት።