የአሦርም ንጉሥ በሆሴዕ ላይ ዐመፅ አገኘ፤ መልእክተኞችን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሴጎር ልኮ ነበርና፤ እንደ ልማዱም በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ግብር አልሰጠምና፤ ስለዚህ የአሦር ንጉሥ ተዋጋው፤ ይዞም በወህኒ ቤት አሰረው።
2 ነገሥት 17:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአሦርም ንጉሥ በምድር ሁሉ ላይ ወጣ፤ ወደ ሰማርያም ወጥቶ ሦስት ዓመት ከበባት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአሦርም ንጉሥ አገሩን በሙሉ ወረረ፤ ወደ ሰማርያም ገሥግሦ ሦስት ዓመት ከበባት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ሰልምናሶር አገሪቱን ወረረና ሰማርያን ለሦስት ዓመት ከበባት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሰልምናሶር አገሪቱን ወረረና ሰማርያን ለሦስት ዓመት ከበባት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአሦርም ንጉሥ በምድር ሁሉ ላይ ወጣ፤ ወደ ሰማርያም ወጥቶ ሦስት ዓመት ከበባት። |
የአሦርም ንጉሥ በሆሴዕ ላይ ዐመፅ አገኘ፤ መልእክተኞችን ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ሴጎር ልኮ ነበርና፤ እንደ ልማዱም በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ግብር አልሰጠምና፤ ስለዚህ የአሦር ንጉሥ ተዋጋው፤ ይዞም በወህኒ ቤት አሰረው።
ሕዝቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ የእስራኤል ንጉሥ የኤላ ልጅ ሆሴዕ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት፥ የአሦር ንጉሥ ስልምናሶር ወደ ሰማርያ ወጣ፤ ከበባትም።