2 ነገሥት 17:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተም ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን አትርሱ፤ ሌሎችንም አማልክት አትፍሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእናንተ ጋራ የገባሁትን ኪዳን አትርሱ፤ ሌሎች አማልክትም አታምልኩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳን አትርሱ፤ ባዕዳን አማልክትንም አታምልኩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳን አትርሱ፤ ባዕዳን አማልክትንም አታምልኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተም ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አትርሱ፤ ሌሎች አማልክትንም አትፍሩ። |
ከእናንተ ጋር የተማማለውን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ፤ አምላክህ እግዚአብሔር የከለከለውን፥ በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ እንግዲህ ተጠንቀቁ።
እናንተንም፦ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን የአሞሬዎናውያንን አማልክት አትፍሩ አልኋችሁ። እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም።”