ኢዮአስም ካህኑን ዮዳሄንና ካህናቱን ጠርቶ፥ “በመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ስፍራዎች ስለ ምን አልጠገናችሁም? ከእንግዲህ ወዲያ ገንዘቡ ለቤቱ መጠገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚያመጡት ሰዎች አትቀበሉ” አላቸው።
2 ነገሥት 12:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህናቱም “ከሕዝቡ ገንዘቡን አንወስድም፤ በቤቱም ውስጥ የተናዱትን አንጠግንም፥” ብለው ተስማሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናቱም ከእንግዲህ ከሕዝቡ ገንዘብ ላለመሰብሰብና ቤተ መቅደሱንም ራሳቸው ላለማደስ ተስማሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱም በዚህ ተስማምተው ቤተ መቅደሱን ለማደስ የነበራቸውን ተግባር አቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናቱም በዚህ ተስማምተው ቤተ መቅደሱን ለማደስ የነበራቸውን ተግባር አቆሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአስም ካህኑን ዮዳሄንና ካህናቱን ጠርቶ “በመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ስፍራዎች ስለ ምን አትጠግኑአቸውም? ከእንግዲህ ወዲያ ገንዘቡ ለቤቱ መጠገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚያመጡት ሰዎች አትቀበሉ፤” አላቸው። |
ኢዮአስም ካህኑን ዮዳሄንና ካህናቱን ጠርቶ፥ “በመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ስፍራዎች ስለ ምን አልጠገናችሁም? ከእንግዲህ ወዲያ ገንዘቡ ለቤቱ መጠገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚያመጡት ሰዎች አትቀበሉ” አላቸው።
ካህኑ ዮዳሄ ግን አንድ ሣጥን ወስዶ መክደኛውን ነደለው፤ በመሠዊያውም አጠገብ ሰው ወደ እግዚአብሔር ቤት በሚገባበት መግቢያ በስተቀኝ አኖረው፤ ደጁንም የሚጠብቁ ካህናት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጣውን ገንዘብ ሁሉ በሚዛን አስገቡ።
“ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኬልቅዩ ወጥተህ ደጃፉን የሚጠብቁ ከሕዝቡ የሰበሰቡትን ወደ እግዚአብሔር ቤት የገባውን ወርቅ ቍጠር።