2 ነገሥት 12:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሠራተኞችም ይከፍሉ ዘንድ ገንዘቡን የሚወስዱትን ሰዎች አይቈጣጠሩአቸውም ነበር፤ በታማኝነት ይሠሩ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሠራተኞቹ እንዲከፍሉ ገንዘቡ የተሰጣቸው ሰዎች ፍጹም ታማኞች በመሆናቸው ተቈጣጣሪ ማድረግ አላስፈለጋቸውም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሥራው ኃላፊነት የተመረጡትም ሰዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ነበሩ ገንዘቡን የሰጡአቸውን ሰዎች አይቆጣጠሩአቸውም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሥራው ኀላፊነት የተመረጡትም ሰዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ነበሩ ገንዘቡን የሰጡአቸውን ሰዎች አይቈጣጠሩአቸውም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ለሚሠሩት ይሰጡት ነበር፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ጠገኑበት። |
ሰዎቹም ሥራውን በመታመን አደረጉ፤ በእነርሱም ላይ የተሾሙት፥ ሥራውንም የሚያሠሩት ሌዋውያን ከሜራሪ ልጆች ይኤትና አብድያስ፥ ከቀዓትም ልጆች ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። ከሌዋውያንም ወገን በዜማ ዕቃ ዐዋቂዎች፥ የነበሩ ሁሉ፥
ወንድሜን ሃናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያንም በኢየሩሳሌም ላይ ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ።
ጌታችን ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፥ “መጋቢ የነበረው አንድ ባለጸጋ ሰው ነበረ፤ ገንዘቡን ሁሉ እንደሚበትን አድርገው በእርሱ ዘንድ ከሰሱት።