ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ቤት ከሚመጣው ገንዘብ ለእግዚአብሔር ቤት የሚሆኑ የብር መዝጊያዎች፥ ጽዋዎችና ጕጠቶች፥ ድስቶችም፥ መለከቶችም፥ የወርቅና የብር ዕቃዎችም አልተሠሩም ነበር።
2 ነገሥት 12:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ለሚሠሩት ይሰጡት ነበር፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ጠገኑበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተከፈለው ግን የእግዚአብሔርን ቤት ለሚያድሱ ሠራተኞች ብቻ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያ ገንዘብ በሙሉ በቤተ መቅደሱ እድሳት ተግባር ላይ ለተሰማሩት ሠራተኞች ብቻ የሚውል ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያ ገንዘብ በሙሉ በቤተ መቅደሱ እድሳት ተግባር ላይ ለተሰማሩት ሠራተኞች ብቻ የሚውል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ቤት ከሚመጣው ገንዘብ ለእግዚአብሔር ቤት የሚሆኑ የብር ጽዋዎችና ጕጠቶች ድስቶችም መለከቶችም የወርቅና የብር ዕቃዎችም አልተሠሩም ነበር። |
ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር ቤት ከሚመጣው ገንዘብ ለእግዚአብሔር ቤት የሚሆኑ የብር መዝጊያዎች፥ ጽዋዎችና ጕጠቶች፥ ድስቶችም፥ መለከቶችም፥ የወርቅና የብር ዕቃዎችም አልተሠሩም ነበር።
ለሠራተኞችም ይከፍሉ ዘንድ ገንዘቡን የሚወስዱትን ሰዎች አይቈጣጠሩአቸውም ነበር፤ በታማኝነት ይሠሩ ነበርና።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሕንጻ ወደ ኋላ እንዳይል ዳዊት ከየሀገሩ በማረካቸውና በሰበሰባቸው በቀደሳቸውም ላይ የተሾሙ ናቸው።
የእግዚአብሔርንም ቤት በሚሠሩት ላይ ለተሾሙት ሰጡ፤ እነርሱም ይጠግኑና ያድሱ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቤት ለሚሠሩ ሠራተኞች ሰጡአቸው።
ይህንም ያለ፥ ድሆች አሳዝነውት አይደለም፤ ሌባ ነበርና፥ ሙዳየ ምጽዋቱንም ሲጠብቅ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ነበርና ስለዚህ ነው እንጂ።