La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መቶ አለ​ቆ​ችም ብልሁ ዮዳሄ ያዘ​ዛ​ቸ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም እያ​ን​ዳ​ንዱ በሰ​ን​በት ይገቡ የነ​በ​ሩ​ትን፥ በሰ​ን​በ​ትም ይወጡ የነ​በ​ሩ​ትን ሰዎች ይዘው ወደ ካህኑ ወደ ዮዳሄ መጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የመቶ አለቆቹም ልክ ካህኑ ዮዳሄ እንዳዘዘው አደረጉ፤ እያንዳንዳቸውም በሰንበት ዕለት ለዘብ ጥበቃ የሚገቡትንና ከዘብ ጥበቃ የሚወጡትን ጭፍሮቻቸውን ይዘው ወደ ካህኑ ወደ ዮዳሄ መጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የጦር መኰንኖቹም ዮዳሄ የሰጠውን መመሪያ በመቀበል በሰንበት ቀን ለዘብ ጥበቃ የሚሰማሩትንና ከዘብ ጥበቃም የሚወጡትን ጭፍሮቻቸውን ጭምር አሰልፈው ወደ እርሱ አመጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የጦር መኰንኖቹም ዮዳሄ የሰጠውን መመሪያ በመቀበል በሰንበት ቀን ለዘብ ጥበቃ የሚሰማሩትንና ከዘብ ጥበቃም የሚወጡትን ጭፍሮቻቸውን ጭምር አሰልፈው ወደ እርሱ አመጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መቶ አለቆችም ካህኑ ዮዳሄ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ፤ ከእነርሱም እያንዳንዱ በሰንበት ይገቡ የነበሩትን፥ በሰንበቱም ይወጡ የነበሩትን ሰዎች ይዘው ወደ ካህኑ ወደ ዮዳሄ መጡ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 11:9
4 Referencias Cruzadas  

የዮ​ዳሄ ልጅ በና​ያ​ስም አማ​ካሪ ነበረ፤ ከሊ​ታ​ው​ያ​ንና፥ ፊሊ​ታ​ው​ያን፥ የዳ​ዊ​ትም ልጆች የፍ​ርድ ቤት አለ​ቆች ነበሩ።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ዮዳሄ ልኮ፥ በኮ​ራ​ው​ያ​ንና በዘ​በ​ኞች ላይ ያሉ​ትን የመቶ አለ​ቆች ወሰደ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አገ​ባ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አማ​ላ​ቸው፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አሳ​ያ​ቸው።


ይህ ሰሎ​ሚ​ትና ወን​ድ​ሞቹ፥ ንጉሡ ዳዊ​ትና የአ​ባ​ቶች ቤቶች አለ​ቆች፥ ሻለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለ​ቆች፥ በቀ​ደ​ሱት በን​ዋየ ቅድ​ሳቱ ቤተ መዛ​ግ​ብት ሁሉ ላይ ተሹ​መው ነበር።


ሌዋ​ው​ያ​ንና ይሁ​ዳም ሁሉ ካህኑ ኢዮ​አዳ ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረጉ፤ ካህ​ኑም ኢዮ​አዳ ሰሞ​ነ​ኞ​ቹን አላ​ሰ​ና​በ​ተም ነበ​ርና እያ​ን​ዳ​ንዱ ከሰ​ን​በት መጀ​መ​ሪያ እስከ ሰን​በት መጨ​ረሻ ሰዎ​ችን ወሰደ።