እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “እንዲህ አድርጉ፤ በሰንበት ቀን ከምትገቡት ከእናንተ ከሦስት አንዱ እጅ በበር ተቀምጣችሁ የንጉሡን ቤት ዘብ ጠብቁ፤
2 ነገሥት 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናንተም በሰንበት ቀን የምትወጡት ሁለቱ እጅ ንጉሥ ያለበትን የእግዚአብሔርን ቤት ጠብቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ እንደተለመደው በሰንበት ዕለት ከዘብ ጥበቃ ነጻ የምትሆኑት ሁለት ሦስተኛው እጅ ግን ንጉሡ ያለበትን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ጠብቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰንበት ቀን ከዘብ ጥበቃ ነጻ የሆኑት ሁለቱ ቡድኖች ግን በንጉሡ ላይ አደጋ እንዳይደርስበት ለመከላከል ቤተ መቅደሱን ይጠብቁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰንበት ቀን ከዘብ ጥበቃ ነጻ የሆኑት ሁለቱ ቡድኖች ግን በንጉሡ ላይ አደጋ እንዳይደርስበት ለመከላከል ቤተ መቅደሱን ይጠብቁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተም በሰንበት ቀን የምትወጡት ሁለቱ እጅ በንጉሥ ዙሪያ ሆናችሁ የእግዚአብሔርን ቤት ጠብቁ። |
እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “እንዲህ አድርጉ፤ በሰንበት ቀን ከምትገቡት ከእናንተ ከሦስት አንዱ እጅ በበር ተቀምጣችሁ የንጉሡን ቤት ዘብ ጠብቁ፤
ሌላውም ከሦስት አንዱ እጅ በሰፊው መንገድ በበሩ በኩል ተቀመጡ፤ ሦስተኛውም እጅ ከዘበኞች ቤት በኋላ ባለው በር ሁኑ፤ ቤቱንም አጽንታችሁ ጠብቁ፤
ንጉሡንም በዙሪያው ክበቡት፤ የጦር ዕቃችሁም በእጃችሁ ይሁን፤ በሰልፋችሁም መካከል የሚገባ ይገደል፤ ንጉሡም በወጣና በገባ ጊዜ ከእርሱ ጋር ሁኑ።”
ወደ እግዚአብሔር ቤት ግን ከካህናትና ከሌዋውያን ከሌዋውያኑም አገልጋዮች በቀር ማንም አይግባ፤ እነርሱ ቅዱሳን ናቸውና ይግቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቅ።