የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት ኢዮሳቡሄም የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል ሰርቃ ወሰደችው፤ እርሱንና ሞግዚቱንም ወደ እልፍኝ ወሰደች፤ ከጎቶልያም ሸሸገችው፤ አልገደሉትምም።
2 ነገሥት 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሰባት ዓመት ልጅ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሰባት ዓመት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአስም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሰባት ዓመት ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአስም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሰባት ዓመት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሰባት ዓመት ልጅ ነበረ። |
የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የአካዝያስ እኅት ኢዮሳቡሄም የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል ሰርቃ ወሰደችው፤ እርሱንና ሞግዚቱንም ወደ እልፍኝ ወሰደች፤ ከጎቶልያም ሸሸገችው፤ አልገደሉትምም።
በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ ልኮ፥ በኮራውያንና በዘበኞች ላይ ያሉትን የመቶ አለቆች ወሰደ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት አገባቸው፤ ከእነርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አደረገ፤ በእግዚአብሔርም ቤት አማላቸው፤ የንጉሡንም ልጅ አሳያቸው።
ኢዩ በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ ነገሠ፤ በኢየሩሳሌምም አርባ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ሳቢያ የተባለች የቤርሳቤህ ሴት ነበረች።
ኢዮስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ከባሱሮት የሆነ የአዳያ ልጅ ይዲያ ነበረች።