የእግዚአብሔር ባሪያ የይሁዳ አለቃ ዘሩባቤልና በይሁዳ ያሉ ሽማግሌዎች የእግዚአብሔርን ቤት በቦታው ይሠሩት ዘንድ የሶርያና የፊንቂስ ገዥ ሲሳኒስና ሳትራቡዛኒስ፥ ከእነርሱም ጋራ ያሉ ጓደኞቻቸው የሶርያና የፊንቂስ ሹሞች ቦታቸውን ይተዉላቸው ዘንድ አዘዘ፤