ሌዋውያንንም በቤተ እግዚአብሔር ሥራ ላይ ሾሟቸው፤ ኢያሱና ልጆቹ፥ ወንድሞቹም፥ ወንድሙ አድያምያልም፥ የኢያሱ ልጅ ሄሜዴቦን፥ የኤልያዳን ልጅ የይሁዳ ልጆች፥ ከልጆቹና ከወንድሞቹ ጋር ሌዋውያንም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት ይሠሩ ዘንድ የሥራ አለቆች ሆነው በአንድነት ተሾሙ።