ከዚህ በኋላም ንጉሡ ዳርዮስ አቅፎ ሳመው፤ እርሱንና ይሠሯት ዘንድ ወደ ኢየሩሳሌም የሚወጡትን ከእርሱ ጋር ያሉትን ሁሉ ይሹ ዘንድ ወደ ግምጃ ቤት አዛዦችና ወደ አለቆች፥ ወደ መሳፍንቱና ወደ መኳንንቱ ሁሉ ደብዳቤዎችን ጻፈለት።