ከዚህ በኋላ ንጉሡ ለጻፈለት ለታሪክ ጸሓፊው ለራቲሞስና ለቤሔልማቴም፥ ለጸሓፊው ለሳሚልዮስም በሰማርያና በፊኒቂስ ለሚኖሩ፥ ከእነርሱ በታች ላሉ፥ ለቀሩትም እንደ ጻፉለት እንዲህ የምትል ደብዳቤን ጻፈላቸው።