ከእነርሱም ውስጥ የፋርስ ንጉሥ አርጤክስስ በይሁዳና በኢየሩሳሌም አውራጃዎች ያስቈጠራቸው አሉ፤ ቤልሞስና ሚጥራዳጢ፥ ጠቢልዮስና ራቲሞስ፥ ቤሔልጤሞስና ጸሓፊው ሲሳዮስ፥ ከነዚህም በታች ያሉ በሰማርያ የሚኖሩ ሁሉ፥ በሌላም ሀገር ያሉ ሁሉ እንዲህ ብለው መልእክት ጻፉ።