La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ቆሮንቶስ 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚህ ወራት ተካ​ክ​ላ​ችሁ እን​ድ​ት​ኖሩ ነው እንጂ ሌላው እን​ዲ​ያ​ርፍ እና​ን​ተን የም​ና​ስ​ጨ​ንቅ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህን የምንለው እናንተ ተቸግራችሁ ሌሎች ይድላቸው ለማለት ሳይሆን፣ ሁላችሁም እኩል እንድትሆኑ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በናንተ ላይ ጫና ይብዛ ለሌሎች ደግሞ ዕረፍት ይሁን ማለቴ አይደለም፤ ነገር ግን ሁላችሁም እኩል እንድትሆኑ ነው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህንንም ስል ሁላችሁም እኩል እንድትሆኑ እንጂ እናንተ በመስጠት ስትቸገሩ ሌሎች እንዲያርፉ ብዬ አይደለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለሌሎች ዕረፍት ለእናንተም መከራ እንዲሆን አይደለም፥ ትክክል እንዲሆን ነው እንጂ፤

Ver Capítulo



2 ቆሮንቶስ 8:13
5 Referencias Cruzadas  

ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ርስት ለሌ​ዋ​ው​ያን የም​ት​ሰ​ጡ​አ​ቸ​ውን ከተ​ሞች እን​ዲህ ስጡ፤ ከብ​ዙ​ዎቹ ብዙ፥ ከጥ​ቂ​ቶቹ ጥቂት ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ወረ​ሱት እንደ ርስ​ታ​ቸው መጠን ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሰ​ጣሉ።”


ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ስንኳ ችግ​ረኛ አል​ነ​በ​ረም፤ ቤትና መሬት ያላ​ቸ​ውም ሁሉ እየ​ሸጡ ገን​ዘ​ቡን ያመጡ ነበር።


ፈቃድ ካለም፥ ሰው በሚ​ቻ​ለው መጠን ቢሰጥ ይመ​ሰ​ገ​ናል፤ በማ​ይ​ቻ​ለ​ውም መጠን አይ​ደ​ለም።


ኑሮ​አ​ችሁ በሁሉ የተ​ካ​ከለ ይሆን ዘንድ፥ የእ​ና​ንተ ትርፍ የእ​ነ​ር​ሱን ጕድ​ለት ይመ​ላ​ልና፥ የእ​ነ​ር​ሱም ትርፍ የእ​ና​ን​ተን ጕድ​ለት ይመ​ላ​ልና።