የመጣኸው ትናንት ነው፤ ዛሬ ከእኛ ጋር ላዙርህን? እኔ ወደምሄድበት እሄዳለሁ፤ አንተ ግን ተመለስ፤ ወንድሞችህንም ከአንተ ጋር መልሳቸው፤ እግዚአብሔርም ምሕረቱንና እውነቱን ያድርግልህ” አለው።
2 ቆሮንቶስ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአባታችን ከእግዚአብሔርና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአባታችን ከእግዚአብሔር፣ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። |
የመጣኸው ትናንት ነው፤ ዛሬ ከእኛ ጋር ላዙርህን? እኔ ወደምሄድበት እሄዳለሁ፤ አንተ ግን ተመለስ፤ ወንድሞችህንም ከአንተ ጋር መልሳቸው፤ እግዚአብሔርም ምሕረቱንና እውነቱን ያድርግልህ” አለው።
መንፈስም በሠላሳው አለቃ በዓማሣይ ላይ መጣ፤ እርሱም፥ “ዳዊት ሆይ፥ እኛ ያንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፥ እኛ ከአንተ ጋር ነን፤ ውጣ አምላክህ ይረዳሃልና ሰላም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ ለሚረዱህም ሰላም ይሁን” አለ። ዳዊትም ተቀበላቸው፤ የጭፍራም አለቆች አደረጋቸው።
በሮሜ ላላችሁ፥ እግዚአብሔር ለሚወዳችሁ፥ ለመረጣችሁና ላከበራችሁ ሁሉ፥ ከአባታችን ከእግዚአብሔር፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
ከአባታችን ከእግዚአብሔር አብ፥ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ከእምነት ጋር ሰላምና ፍቅር ለወንድሞቻችን ይሁን።
በቈላስይስ ላሉ ቅዱሳንና በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ ወንድሞቻችን፥ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስም ሰላምና ጸጋ ለእናንተ ይሁን።
ጳውሎስና ስልዋኖስ ጢሞቴዎስም፥ በእግዚአብሔር አብ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም ወደምትሆን ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ቤተ ክርስቲያን፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋ ሰላምም ለእናንተ ይሁን።