La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ዜና መዋዕል 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰሎ​ሞ​ንም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆኑ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያሉ እስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ በዚያ ጊዜ ሰባት ቀን በዓል አደ​ረጉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ጊዜም ሰሎሞን ዐብረውት ከነበሩት ከእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ጋራ ለሰባት ቀን በዓሉን አከበረ፤ ሕዝቡም ከሐማት መግቢያ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ ካለው ምድር የመጣ እጅግ ታላቅ ጉባኤ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆኑ፥ ከሐማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ ያሉ እስራኤል ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ ሰባት ቀን በዓል አደረጉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና እስራኤላውያን ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ሸለቆ ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰሎሞንም ከእርሱም ጋር እጅግ ታላቅ ጉባኤ የሆኑ፥ ከሐማት መግቢያ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ ያሉ እስራኤል ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ ሰባት ቀን በዓል አደረጉ።

Ver Capítulo



2 ዜና መዋዕል 7:8
19 Referencias Cruzadas  

በዚ​ያ​ችም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤


ይኸ​ውም አታ​ሚን በሚ​ባል በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ነበር።


በዚ​ያም ዘመን ሰሎ​ሞን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠ​ራው ቤት ውስጥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፥ ደስ​ታም እያ​ደ​ረጉ ሰባት ቀን በዓ​ሉን አከ​በሩ።


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር የቂ​ጣ​ውን በዓል ያደ​ርጉ ዘንድ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ብዙ ሕዝብ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እጅ​ግም ታላቅ ጉባኤ ነበረ።


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ታላቅ ደስታ ሆነ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ከዳ​ዊት ልጅ ከን​ጉሥ ሰሎ​ሞን ዘመን ጀምሮ እን​ደ​ዚህ ያለ በዓል በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ተ​ደ​ረ​ገም ነበር።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር በበ​ዓሉ ጊዜ ወደ ንጉሡ ወደ ሰሎ​ሞን ተሰ​በ​ሰቡ።


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በበ​ዓሉ ሰባት ቀኖች፥ የኃ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን ከዘ​ይቱ ጋር እን​ዲሁ ያቅ​ርብ።”


የም​ዕ​ራ​ቡም ድን​በር ከደ​ቡቡ ድን​በር ጀምሮ እስከ ሐማት መግ​ቢያ አን​ጻር ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆ​ናል። የም​ዕ​ራቡ ድን​በር ይህ ነው።


“የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ እነሆ እኔ የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ች​ሁን ሕዝብ አስ​ነ​ሣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥” ይላል የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ከሐ​ማት መግ​ቢያ ጀም​ረው እስከ ዐረባ ወንዝ ድረስ ትገቡ ዘንድ አይ​ፈ​ቅ​ዱ​ላ​ች​ሁም።


የአ​ይ​ሁ​ድም የዳስ በዓ​ላ​ቸው ደርሶ ነበር።