ራፋስቂስም አላቸው፥ “ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ታላቁ ንጉሥ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ይህ የምትተማመንበት መተማመኛ ምንድን ነው?
2 ዜና መዋዕል 32:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም እንዲህ ይላል፦ እናንተ በማን ተማምናችሁ በኢየሩሳሌም ምሽግ ትቀመጣላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም እንዲህ ይላል፤ በተከበበችው በኢየሩሳሌም እስከዚህ የቈያችሁት በማን ተማምናችሁ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም እንዲህ ይላል፦ ‘እናንተ በማን ተማምናችሁ በኢየሩሳሌም ምሽግ ትቀመጣላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እኔ የአሦር ንጉሠ ነገሥት የሆንኩ ሰናክሬም፥ በእኔ ሠራዊት በተከበበችው በኢየሩሳሌም ለመቈየት ያሰባችሁት በማን ተማምናችሁ እንደ ሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም እንዲህ ይላል ‘እናንተ በማን ተማምናችሁ በኢየሩሳሌም ምሽግ ትቀመጣላችሁ? |
ራፋስቂስም አላቸው፥ “ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ታላቁ ንጉሥ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ይህ የምትተማመንበት መተማመኛ ምንድን ነው?
አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ያድነናል እያለ ለራብ፥ ለጥምና ለሞት አሳልፎ ይሰጣችሁ ዘንድ የሚያሳስታችሁ ሕዝቅያስ አይደለምን?
ከዚህም በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር በለኪሶ ፊት ሳለ ባሪያዎቹን ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስና በኢየሩሳሌም ወደ ነበሩ ወደ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ሲል ላከ፦
ራፋስቂስም አላቸው፥ “ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ በማን ትተማመናለህ?