የልጆቹና በእርሱ ላይ የተደረገው ነገር፥ የእግዚአብሔርንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ በነገሥታቱ የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል። ልጁም አሜስያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
2 ዜና መዋዕል 25:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሜስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱ ኢዮዓዲን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሜስያስ በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ። እናቱም ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሜስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሀያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሜስያስ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ሲሆን ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ኻያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤ እናቱ ይሆዓዲን ተብላ የምትጠራ የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሜስያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ሀያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች። |
የልጆቹና በእርሱ ላይ የተደረገው ነገር፥ የእግዚአብሔርንም ቤት ማደሱ፥ እነሆ በነገሥታቱ የታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል። ልጁም አሜስያስ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።