ከሦስት አንድ እጅም በንጉሡ ቤት ሁኑ፤ ሌላውም ከሦስት አንድ እጅ በመካከለኛው በር ሁኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ይሁኑ።
2 ዜና መዋዕል 23:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ እግዚአብሔር ቤት ግን ከካህናትና ከሌዋውያን ከሌዋውያኑም አገልጋዮች በቀር ማንም አይግባ፤ እነርሱ ቅዱሳን ናቸውና ይግቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተረኛ ከሆኑት ካህናትና ሌዋውያን በቀር ማንም ሰው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አይግባ፤ እነርሱ የተቀደሱ ስለ ሆኑ ይግቡ፤ የቀሩት ሰዎች በሙሉ ግን፣ እግዚአብሔር ያዘዘውን ይጠብቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጌታ ቤት ግን ከካህናትና ከአገልጋዮቹ ሌዋውያን በቀር ማንም አይግባ፤ እነርሱ ቅዱሳን ናቸውና ይግቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ ግን የጌታን ሕግ ይጠብቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአገልግሎት ላይ ከሚገኙት ካህናትና ሌዋውያን በቀር ማንም ሰው ወደ ቤተ መቅደሱ መግባት የለበትም፤ ካህናትና ሌዋውያን ግን ለእግዚአብሔር የተለዩ ስለ ሆኑ መግባት ይፈቀድላቸዋል፤ የቀሩት ሰዎች የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመፈጸም ከቤተ መቅደሱ ውጪ ይሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ እግዚአብሔር ቤት ግን ከካህናትና ከአገልጋዮቹ ሌዋውያን በቀር ማንም አይግባ፤ እነርሱ ቅዱሳን ናቸውና ይግቡ፤ ሕዝቡም ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ይጠብቅ። |
ከሦስት አንድ እጅም በንጉሡ ቤት ሁኑ፤ ሌላውም ከሦስት አንድ እጅ በመካከለኛው በር ሁኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ይሁኑ።
ሌዋውያንም የጦር መሣሪያቸውን በእጃቸው ይዘው ንጉሡን በዙሪያው ይክበቡት፤ ወደ ቤቱም የሚገባ ይገደል፤ ንጉሡም ሲገባና ሲወጣ ከእርሱ ጋር ሁኑ።”